ካሊ ማናት? ምንድን ናት?

KaliTimes logo banner
KaliTimes logo banner

ካሊ በሶማሌ ክልል የምትገኝ የሶማሌ ሕዝብ ኢትዮጵያዊነት የታወጀባት ታሪካዊ መንደር ናት።

እንግሊዝ የኦጋዴንን መሬት ለኢትዮጵያ እኤአ በ1954 ከመመለሷ በፊት ካሊ በተባለ ቦታ ላይ የኢትዮጵያ ሶማሌ የጎሳ መሪዎችን ሰብስበዋቸው ነበር፡፡ በዚያ ሸለቆ ውስጥ የተሰባሰቡ የጎሳ መሪዎች ሦስት አማራጭ እንደቀረበላቸው በወቅቱ ልጆች ሆነው ነገሩን የተከታተሉና ከሽማግሌዎቹ የሰሙ የሀገር ሽማግሌዎች በቦታው ላይ ሲናገሩ ሰምቻቸዋለሁ፡፡ ከታላቋ ሶማሊያ ጋር ትዋሐዳላችሁ፣ ከኢትዮጵያ ጋር ትዋሐዳላችሁ ወይስ ራሳችሁን ትችላላችሁ፡፡ እንዲያውም የእንግሊዙ መኮንን አንድ ከሸማ የተሠራ ልብስ አምጥቶ በቁጥቋጦው ላይ ጣለውና መልሶ አነሣው፡፡ ልብሱ በቁጥቋጦው እሾህ ተቀዳዶ ነበር፡፡ ‹ኢትዮጵያ ዕጣ ፈንታዋ እንዲህ ነው› አላቸው፡፡ እነዚያ የጎሳ መሪዎች ግን ኢትዮጵያ ድኻ፣መንግሥቷም የማይስማማን መሆኑን እናውቃለን፡፡ ነገር ግን ከእርሷ ተገንጥለን አንወጣም› ማለታቸውን ሽማግሌዎቹ ተናግረዋል፡፡

********

more recommended stories