የኢፈዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶር አብይ አህመድ የመጀመሪያ የስራ ጉቡኝታቸው በነገ እለት በጅግጅጋ ያደርጋሉ

 

ጅግጅጋ(kalitimes)አርቢ፤መጋቢት 28/2010ዓ.ም.በኢፈዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶር አብይ አህመድ የሚመራ ከፈተኛ የመንግስት ልዕኳን ቡዱን በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል መንግስት ርዕሰመዲና በሆነችው በጅግጅጋ ከተማ እንደሚጎበኙ ተገለጸ።

ጠቅላይ ሚኒስቴሩ ዶር አብይ ከኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል መንግስት፤ከኢ.ሶ.ህ.ዴ.ፓ. ከፍተኛ አመራር፤ከሀገር ሽማግሎች፤ከገራዶች፤ኡጋሶች፤ወጣቶችና ሴቶች እንድሁም ከሌሎች የህብረተሰብ ክፍሎች በሀገሪቱ ወቅታዊ ጉዳዮችና በጸጥታ እንደሁም በሌሎች ወሰኝ ርዕሰጉዳዮች ዙሪያ ከህዝቡ እንደሚያነጋገሩ ይጠበቃል።

በተጨማሪም በኦሮሚያና በኢትዮሶማሌ ክልሎች ግጭት ሳቢያ የተፈናቀሉ ዜጎች ያሉበት መጠሊያ ጣቢያዎች እንደሚጎበኙና ተፈናቃዮቹ ለአንደና ለመጨረሻ የመልሶ ማቋቋም እልባት እንደሚያገኙና በመደበኛ ኑሮኣቸው እንደሚመለሱ ይጠበቃል።

የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ህዝብና መንግስት ለኢፈዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትራቸው ዶር አብይ አህመድን በኢትዮጵያ ታሪክ ታይቶና ተሰምቶ የማይታወቅ የእንግዳ ተቀባይነት አቀባበልና ክቡር ግብዣ ያደርጉለታሉ በዶር አብይ አህመድ የሚመራ የኢፈዴሪ መንግስት አላማም በጽኑ ያስፈጽማሉ ተብሎ ይጠበቃል።

*******

%d bloggers like this: