በመላው የሶማሌ ህብረተሰብ እኩልነት የሚፈጠር የዘመኑ ሰርግ ሥነስርዓት ልዩ ዝግጅት በጅግጅጋ ከተማ ተካሄ

ጅግጅጋ,Kalitimes. አርብ፤ሚያዝያ 5 ቀን 2010ዓም. ከዘመናት በፊት በሁሉም የሶማሌ ማህበረሰብ ባህል እና ልማድ እንዲሁም ሃይማኖታዊ ሥርዓት ውጭ የገጠማችሁን የረሃብ አደጋ ለመከላከል የሞተ እንስሳቶችን የበከተ በልታችኋል ተብለው የገቦያ ጎሳ እንደተገለሉ በአፈ ታሪክ ይነገራል። በዚህም አፈታሪክ ምክንያት ለዘመናት በሶማሌ ጎሳዎች መድሎ እና መገለል ደርሶበት የሥነ ልቦና ችግር በገቦያ ማህበረሰብ ላይ እንደደረሰም ይነገራል። የገቦዬ ጎሳ ማህበረሰብ ከሌላው የሶማሌ ጎሳዎ ች በሃይማኖት ፣ በባህል እና በወግ አንድ ሆኖ ሳለ በደረሰበት መገለል የበታችነት ስሜት ተፅዕኖ በማህበረሰቡ ላይ ከማምጣቱም በተጨማሪ ማህበረሰቡ አነስተኛ የሥራ ዓይነት አድርጎ በሚወስደው የሥራ ዘርፎች  በመሰማራት ህይወታቸውን ማቆየት ችለዋል።

የገቦያ ማህበረሰብ ልክ እንደሌሎቹ የሶማሌ ጎሳዎች ከተለያዩ ጎሳዎች ጋር መጋባት የማይችል ሲሆን ገቦዬዎች እርስ በእርሳቸው ትዳር የሚመሰርቱበት ምክንያትም የሌላው የሶማሌ ጎሳ ልጆች በጋብቻ ከገቦያ ጋር እንዲመሰርቱ ባለመፈለጋቸውም ነው። ይህንን በገቦያ ላይ የደረሰውን ከፍተኛ ጫና እና መገለል ከኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ለአንዴ እና ለመጨረሻ ጊዜ ለማስወገድም የታሰበው ጠንካራ አቋምና የክልሉ መንግስት እቅድ ዛሬ ላይ መልካም ውጤት እያመጣ መሆኑንም መረጃዎቹ ያመላክታሉ።  ይህ ገቦያ ማህበረሰብ በሥራ የሚናቁና ከአሁን በፊት የትምህርት እድል ያልተሰጣቸውን በመሆናቸው የክልሉ መንግስት ለገቦዬ ማህበረሰብ የስራ እድል የሚፈጠርላቸውን በርካታ መድረኮች በማዘጋጀት እንድሁም በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል መንግስት ፕሬዝዳንት ክቡር አቶ አብዲ መሀሙድ ባደረጉት ተነሻነትና ያላ ለሰለሰ ጥረት በክልሉ  የሚኖሩና የክልሉ ህዝብ የሆኑና እንዲሁም በሥራ እንዱስተሪ ፈርቀዳጭ የሆኑ ገቦዬ ማህበረሰብ  በሚፈጸሚባቸው የንቀት ቃላት መቆም እንዳለበት በተደጋጋሚ መናገራቸውን ይታወሳል።

በተጨማሪም ክቡር ፕሬዝዳንቱ በገቦዬ ማህበረሰብ ላይ በሶማለኛ ቋንቋ የተለያዩ ስያሜዎች በመሰጠት ሲገለሉ የነበሩ መሆናቸው በተለያዩ ውይይት መድረኮች በማንሳት ስያሜያዎችሁ በስህተት የተጠቀሙና በተፈጥሮ ችግር  የለለባቸው መሆናቸው በመግለጽ  ለምሳሌ ያህል “ሚድጋን” የሚለው ቃል በድሮ በእንስሳት አደን ጊዜ ሲጠቀሚበት የነበረ ቃል ሲሆን ትርጉሙ “ቀስት ማስቀየስ”ሲሆን “ገቦየ” የሚለውም “የቀስት መያዣያ” ሲሆን  “ቱማል” የሚለው ቃልም “ላብ አደር ወይም ቀጥቃጭ” የሚል ትርጉም እንዳለውም አብራርቷል።

በሌላ በኩል በቅርቡ በአፍዴር ዞን በራሶ ወረደ በተካሄደው 11ኛው የኢትዮጵያ ሶማሊ ክልል ህዝብና መንግስት የጋራ ምክክር መድረክ በሶማሌ ጎሳዎች መካከል አንዱ ጎሳ ከሌላው ጎሳ ማብለጥ ወይም አንዱ ጎሳ ከሌላው ማያንስ እንደለለ እና በእምነት፤በባህልና በህገመንግስት መሰረት ሳያደርግ በሶማሌ ማህበረስብ ዘንድ የነገሰውና በገቦዬ ማህበረሰብ ላይ የሚደረገው ትርጉም ንቀት እንድቀር በፅኑ እምነት ፀድቋል።በዚህም የክልሉ ባላሀብቶች፤የመንግስትና የግል ሰረተኞች እንዲሁም በክልሉ የሚሰሩ ለጋሽ ድርጅቶች ባሰባሰቡ ከፍተኛ ባጄት ከገቦየ ጎሳ ትዳር የሚመሰረቱ ወጣቶችና ከሌላ ጎሳዎች ትዳር የሚመሰረቱ የገቦዬ ወጣቶችን የመኖሪያ ቤትና ማንቀሻቀሻ ሀብት ባላቤት እንዲሆኑ ምክንያት ሆኗል።በዚህ ረገድ በምድረ ሶማሌ ዘንድ ታይቶና ተሰምቶ በማይታወቅ መልኩ ለ29 ጥንዶች የዘመኑ ሰርግ ሥነስርዓት ተዘጋጅቶለታል።መድረኩ በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ርዕሰመዲና በሆነችው በጅግጅጋ ከተማ በአርበኛው ሰይድ መሀመድ አደራሽ መላው የሶማሌ ማህበረሰብ ቀልብ በሳበ መልኩ ተዘጋጅተዋል።

በዚህ መሰረት በጅግጅጋ የተካሄደውና ሁሉም የሶማለኛ ቋንቋ ተናጋሪዎችና መላው የሶማሌ ህዝብ እኩልነትና አንድነት እንደሁም አንድ አቋም የፈጠረው የዘመኑ የሰርግ ሥነስርዓት ልዩ ዝግጅት የክልሉ መንግስት ከፍትኛ አመራር አካላት የክልሉርዕሰመስተዳደር ክቡር አቶ አብዲ መሀሙድ፤የክልሉ ም/ፕሬዝዳንቶች፤ሀገር ሽማግሌዎች ፤የክልሉ መንግስት ሰረተኞች ፤የእምነት አባቶች ፤ወጣቶች ፤ሴቶችና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው ክቡር እንግዶችም ተገኝተዋል።

በዝግጅቱ ላይም የተለያዩ የሶማሌ ባህላዊ ጭፈራዎችና የሶማሌ ባህላዊ ሙዚቃዎች  እንደ “ዳንቶ’ እንድሁም የሶማሌ ባህላዊ ዘርግ ስርዓት  ልዩ፤ድንቅና ብቸኛ የሚያደርገው የፖሊስና ዳኛ ባህላዊ የእንቆቅልሽ ጥያቄና መልስ ውድድርም በፖሮግራሙ ተካትተዋል።

በተጨማሪም በዝግጅቱ ማጠናቀቅያ ላይ ወሳኝ ንግግር ያደረጉት የኢ.ሶ.ክ.መ.ፕሬዝዳንት ክቡር አቶ አብዲ መሀሙድ ኡመር  ይህ እርምጃ በብሔሬሰቡ ባህል፤ወግና በእስልምናና በክርስትና እምነቶች እንድሁም በምንተዳደረው ህገመንግስታችንም መሰረት ሳያደርግ በሶማሌ ማህበረሰብ ዘንድ ለዘመናት ሲወርድ ሲዋረድ የመጣውን የዘር ማግለልና የእርስ በእርስ  ትርጉም አልባ የመናናቅ አመለካከትን የሚያጠፋ ታላቅ እርምጃ ነው ብሏል።አያይዞም በቀንድ አፍሪካና በአምስቱ ዓለም አህጉራት ያሉት ሶማሌ ህዝቦች በራሳቸው ፈላጎትና ምርጫ ከተለያዩ የሶማሌ ጎሳዎችና ከገቦያ ጎሳ የተጋቡ 29 ጥንዶች በጅግጅጋ ከተማ የተደረገለት የክፍለ ዘመኑ ሰርግ ሥነ-ስርዓት ልዩ ዝግጅት እንደ ምርጥ ተሞክሮ በመወሰድ በብሔረሰቡ ውስጥ የሚታዩ ጎጂ ልማዳዊ ድርግቶችና የዘር ማግለል አመለካከቶችን እንድወገዱ ፕሬዝዳንቱ አሳስቧል። በተጨማሪም ሶማለኛ ቋንቋ የሚናገሩ ጎሳዎች ሁሉም የሰው ልጅ ፍጡር እስከ ሆኑ ድረስ እኩል እንደሆኑና አንድ ጎሳ የበታች  አንዱን ደግሞ የበላይ የሚያደርጉ ሁኔታዎችና ምክንያትም እንደለለ ክቡር ፕሬዝዳንቱ አስረድቷል። በመጨረሻም ፕሬዝዳንት አብዲ መሀሙድ ከገቦዬ ጎሳና ከሌሎች የሶማሌ ጎሳዎች በራሳቸው ፈላጎት ተጋብቶ በክልሉ ርዕሰመዲና በአማረና ደመቀ መልኩ የዘመኑ ሰርግ ሥነስርዓት ልዩ ዝግጅት የተደረገላቸው ጥንዶች ትዳር የተባረከና የተሳከ ትዳር እንድሆንላቸው መርቋል።

ይህ የዘመኑ ሰርግ ሥነ-ስርዓት ልዩ ዝግጅት በክልሉ ዘርፈ ብዙ የልማት፤የሰላምና የመልካም አስተዳደር ስራዎች የተከናወነባቸው ወቅት እንዲሁም በቅርቡ የተሰየመው የኢፌደሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ የመጀመሪያ የስራ ጉቡኝታቸው በክልሉ ባደረጉበት ወቅት በከሊ አደራሽ ባደረጉት ንግግር የሀገራችን ሉዓላዊነትና ዳር ድንበሩን የጠበቁ የኢትዮጵያ ሶማሌ ጀግኖች እንደ አርበኛው ሰይድ መሀመድ አብዲሌና እንደ ጀግናው ደጃዝማች  ኡመር ሰመተር እንደሚኮራባቸውና ኢትዮጵያም ካለ እነርሱ የማይታሰብ እንደሆነች በተናገሩት ወቅት በመጋጠሙ የሰርጉ ሥነስርዓት አደምቋል።የዘገበው ምንጭ:-ESRSMassmedia agency official page

%d bloggers like this: