የኢ.ሶ.ክ. ወጣቶች በክልሉ የተመዘገቡት የፅጥታና ልማት አውተራት የሚደግፉበት ሰልፎች በሁሉም የክልሉ ዞኖች አካሄዱ

 

  

ዋርዴር kalitimes.com እሁድ ሚያዝያ 28/2010ዓም.የአትዮጵያ ሶማሌ ክልል ከ7 አመታት በፊት በክልሉ ስለነበረው የሰላም እጦት ውጣ ወረዶች ምክንያት የክልሉ ዞኖች፤ወረዳዎችና ቀበሌዎች አንዱ ከሌላኛው ጋር ትስስር እንዳልነበረ ይታወቃል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ በክልሉ ስለነበረው የንጹህ መጠጥ ውሃ እጥረት ህይወት ያለው የሰው ልጅና እንስሳትም በውሃ ጥማት ይሞቱ እንደነበሩ የማይካድ ሀቅ ነው። በክልሉ የሚገኙ ከተሞች ገፅታም ደግሞ ከመንደር በታች እንደነበሩ ይታወሳል። በዚህ ረገድ በክልሉ የልማት ዋና እንቅፋትና ተግዳሮት የነበርው የሰላም እጥረትና የፀጥታ መደፍረስ በክልሉ ወጣቶች በተነደፈው የለውጥ ሃሳቦች የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ሌሎች ክልሎች የደረሱበት የለውጥ ታርታ ለማሰለፍ በክልሉ ጠንካራ የፀጥታና የዘላቂ ልማት ስተራቴጂዎና እቅዶች በመነደፍ የህዝቡ አንደኛ ጠላት የነበረውን ደህነት እንዲቀረፍና ማህበረሰቡ በሰላም ወጥቶ በሰላም እንድገባ ምክንያት ሆኗል።

በተጨማሪም የክልሉ ቆራጥ ወጣት አመራሮች በክልሉ ስለነበረው የሰላም ማደረፍና የመስረተ ልማት አውተሮች እጥረት ለመቅረፍ የነደፉት የዘላቂ ሰላምና የህዳሴ ጉዞ ስተራቴጅዎች እንደሁም የክልሉ ወጣቶች የቀረጹት የረጅም ራዕይ እቅዶች በጥቅት አመታት ውስጥ እዉን አደርገዋል።

በመሆኑም የክልሉ ህዝብ በተለይ የክልሉ ሄጎ/የወጣቶች ጉም በትንሽ አመታት ውስጥ የክልሉ መንግስትና የክልሉ መሪ ድርጅት ኢሶህዴፓ በአጠቃላይ በክልሉ ያከናወኑት የንፁህ መጠጥ ውሃ ተደራሽነት᎓የትራንስፖርት መስረት ልማት እንደ ትላልቅ ድልድዮች፤የትምህርት ተደረሽነት᎓የጤና አገልግሎት ማስፋፋትና የተፋሰስና የመስኖ ግብርና እንዲሁም የወጣቶች የሥራ ዕድል ፈጠራ፤የሴቶች የፖለቲካዊ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተሳትፎ በማሳደጋቸውና የቅርቡ በክልሉ አንዳንድ አከባቢዎች በኢሊኖ የአየር ለውጥ ምክንያት በተከሰተው ድርቅን አስመልክቶ የክልሉ መንግስትና የክልሉ መሪ ድርጅት ኢሶህዴፓ በሰጡት ፈጣን ምላሽ እና የመሳሰሉት መልካም ተግባራትን የሚደገፍበት ሰላማዊ ሰልፎች በሲቲ ዞን በቀዳሚነት ከተጀመረ በኋላ በአጠቃላይ በክልሉ ዞኖች፤ወረዳዎችና ከተማ አስተዳደሮች በክልሉ ወጣቶች የሚመራ ሰፊ ሰላማዊ ሰልፍ ተካሄደዋል።

የኢ.ሶ.ህ.ዴ.ፓ.ማዕከላዊ ኮሚቴ አባልና የአርብቶ አደር ማህበረሰብ ልማት ፖሮጀክት ፅ/ቤት ሃላፊ አቶ አብዲሀኪም ኢጋል ኡመር የክልሉ ወጣቶች በቀዳሚነት በሲቲ ዞን  ያካሄዱትና የክልሉ መንግስትና የክልሉ መሪ ድርጅት ኢሶህዴፓ መልካም ክንዋኔዎች የሚደገፍበት ስላማዊ ሰልፍ በክልሉ በሌሎች የክልሉ ዞኖች እንድያካሄዱ ማሳሰባቸውም ይታወሳል። በዚህም በክልሉ የሚገኙ በ11 ዞኖች፤ 93 ወረዳዎችና በ6ቱ ከተማ አስተዳደሮች የክልሉ ልማት፤ሰላም፤የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታና የመልካም አስተዳደር ሥራዎች የሚደገፍበት በርካታ የልማት ሰልፎች ተካሄደዋል።

በዚህ ረገድ በዶሎ ዞን ርዕሰ መዲና በሆነችው በዋርዴር ከተማ ከሰልፈኞች ጋር ንግግር ያደረጉት የክልሉ ም/ርዕሰ መስተዳደርና የእርሻና ተፈጥሮ ሀብት ቢሮ ኃላፊ ክብርት ወ/ሮ  ሱኣድ አህመድ ፋራህ በዋርዴር ከተማ የተካሄደው ሰላማዊ ሰልፍ የክልሉ ሰላም፣ ልማትና የአስተዳደር ሽግሸግ ህዳሴን የሚደገፍበት እንደነበረ ገልጿል። በዋርዴር ከተማና አከባቢዎች የሚኖሩና በአንድ ላይ የተሰባሰቡ ሄጎ የማዕበል ወጣቶች በበኩላቸው ከመቼም በላይ በክልላቸው የተጀመሩ የመስረተ ልማት ሥራዎች እጅግ ደስተኛ ከመሆናቸው ባሻገር ሁሌ የክልሉ መንግስትና የክልሉ መሪ ድርጅት ኢሶህዴፓ ጎን እንደሚቆሙ እንዲሁም የሃገሪቱ ብሎም የክልሉ የጸጥታና የህዳሴ ግስጋሴን ዘብ እንደሚሆኑ አረጋግጧል።

በተመሳሳይም በቆራሄይ፤ በሸቤሌ፤ በጀረር፤ በአፍዴር፤ በሊባን፤ በዳዋ፤ በኖጎብና በኤረር ዞኖች የሰላም፤የልማትና የህዳሴ ሰላማዊ ሰልፎች በሰፊው የተካሄዱት ሲሆን በጎዳናዎቹ ላይ የኢሶህዴፓ ከፍተኛ አመራር አካላት ወሰኝ ንግግሮች አደርገዋል። በመጨረሻም በሰልፎቹ የተሳተፉት የማህበረሰብ ክፍሎች በክልሉ የተጀመሩ የመስረተ ልማት ሥራዎች እጅግ ደስተኛ መሆናቸውና ሁሌም የክልሉ መንግስትና የክልሉ መሪ ድርጅት ኢሶህዴፓ ጎን እንደሚቆሙና የሃገሪቱ የጸጥታ፤ልማትና የህዳሴ ትራንስፎርሜሽን ጉዞን ዘብ እንደሚሆኑ ቃል ገብተዋል።

more recommended stories