በአውበሬ ከተማ ሲካሄድ የነበረው 12ኛው የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ህዝብና መንግስት ምክክር መድረክ ተጠናቀቀ

አውበሬ: KALITIMES.COM.ማክሰኞ፤ ግንቦት 07/2010 ዓ.ም 12ኛው የኢትዮጵያ ሶማሌ  ክልል ህዝብና መንግሥት በፋፈን ዞን የአውበሬ ወረዳ መዲና በሆነችው በአውበሬ ከተማ ለሶስት ቀናት ያህል በሠላም ፣ በልማት ፣ በመልካም አስተዳድር እና በህዳሴ ትራንስፎርሜሽን ዙሪያ ሲያካሂድ የነበረውን የጋራ ምክክር መድረክ በደመቀና በአማረ ሁኔታ ማጠናቅቁ ተገለፀ። በምክክር መድረኩም ከክልሉ 11 ዞኖች ፣ ከ6ቱ የከተማ መስተዳደሮች እና ከ93 ወረዳዎች የተውጣጡ ከ3000 በላይ በሚሆኑ የማህበረሰብ ክፍሎች እንደ  የአገር ሽማግሌዎች ፣ የሃይማኖት አባቶች ፣ ወጣቶችና ሴቶች እና ሌሎች እንግዶችም በድምቀት ተካሂዷል፡፡

በተጨማሪም በ12ኛው የኢትዮጵያ ሶማሌ መንግስትና ህዝብ ምክክር መድረክ ላይ የኢ.ሶ.ክ.መ ፕሬዝዳንት ክቡር አቶ አብዲ መሀሙድ ኡመር ፣ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ፣ የክልሉ መሪ ድርጅት ኢሶህዴፓ ከፍተኛ አመራር አካለት ፣ የክልሉ ም/ቤት አፈጉባኤ ፣ የኢሶህዴፓ ድርጅት ጉዳዮች ዘርፍ ኃላፊ አቶ መሀመድረሺድ ኢሳቅ ፣ የክልሉ ም/ፕሬዝዳንቶች ፣ የክልሉ መንግስት ቢሮ ኃላፊዎች እና ም/ቢሮ ኃላፊዎች የተሳተፉ ሲሆን ከተለያዩ የዓለም አህጉራትና ሃገራት የተውጣጡ ትውልደ ኢትዮጵያዊያንና የክልሉ ተወላጅ ዲያስፖራ አባላት ፣ የክልሉ ባህል ቡድኖች እና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው የክቡር እንግዶችም ተካፍለዋል፡፡

በሌላ በኩል በጉባኤው የታደሙትና ከፋፈን ዞን የቀብሪበያህ ፣ የአራርሶ እና የሙላ ወረዳዎች ሀገር ሽማግሌዎች ፣ የሃይማኖትት አባቶች ምሁራን እና ወጣቶች በጉባኤው ላይ በሶማሌ ብሔረሰብ የባህላዊ ጎሳ መሪ አመራረጥን ሥነ ስርዓት በመከተል የአቡስጉል ጎሳ ሀገር ሽማግሌዎች አባል የነበሩት አቶ አብዲከሪም ቀሊንሌ የአቡስጉል ጎሳ መሪና ሀገር ሽማግሌ አድርጎ ሱልጣን አብዲከሪም ቀሊንሌን ሰይሟል።

በተጨማሪም የአውበሬ ወረዳ ሃገር ሽማግሌዎች በአውበሬ ወረዳና አካባቢዎቿ በሚታወቀው በባህሉ መደበኛ እውቀት እና ትምህርትን የያዙን ውድ መጽሃፍት በስጦታ ኢ.ሶ.ክ.መ ፕሬዝዳንት ክቡር አቶ አብዲ መሀሙድ ኡመር አበርክተውላቸዋል። የአውበሬ ሀገር ሽማግሌዎችና ማህበረሰብ ከጥንት ጀምሮ ያቆዩትን የትምህርትና እውቀት ባህል በማመስገን በአውበሬና አካባቢዎቿ የሚኖሩ ህዝቦች ከጥንት እስከ አሁኑ ታሪክ  የተማሩ ዜጎችን በማፍራት የሚታወቅ ህብረተሰብ መሆኑንም ፕሬዝዳንቱ ገልጿል።

በመጨረሻም የአውበሬ ወረዳ ነዋሪዎች ከሁሉም የክልሉ አስተዳደራዊ መዋቅር ለተውጣጡ የጉባኤው ታዳሚዎች ላደረጉት አቀባባልና መድረኩን በአማረ ሁኔታ በማስተናገዳቸው እንዲሁም ላሳዩት እንግዳ ተቀባይነት ፕሬዝዳንት አብዲ መሀሙድ የላቀ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

 

%d bloggers like this: