በኢ.ሶ.ክ.የአርብቶ አደሩ ማህበረሰብ ህይወት ለማሻሻል የተከናወኑ አመርቂ ስራዎች ለሌሎች ክልሎች ተምሳሌት መሆን እንደሚችል የልዩ ድጋፍ ቦርድ ይፋ አደረገ

ጅግጅጋ(KALITIMES)ግንቦት 28/2010ዓ.ም. የፌደራልና  አርብቶ አደር ልማት ጉዳዮች ሚኒስቴር የአርብቶ አደሩ ህብረተሰብን ህይወት ለማሻሻል በዘርፉ የተከናውኑ ስራዎች ያሉበት ሁኔታ በየጊዜው በሃገሪቱ ም/ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን በሚመራው የፌደራልል ዩድጋፍ የሚሹ ቦርድ ከተለያዩ ባለድርሻ አካላትጋር በመተባበር እንደሚገመገም ይታወቃል።

በዚህም የ2010 የበጀትአመት የ10 ወራት የስራ አፈፃፀምን በአዲስ አበባ የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ፕሬዝዳንት ክቡር አቶ አብዲ ሙሀሙድ ኡመርን ጨምሮ የሌሎች ልዩ ድጋፍ የሚሹ ክልል ፕሬዝዳንቶች በተገኙበት  ተገምግሟል።

በግምገማው መሰረትም በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል የሚኖሩ የአርብቶ አደር ዜጎችን ህይወት ለማሻሻል ክልሉ መንግስት ያከናወናቸው የማህበራዊና ኢከኖሚያዊ ስራዎች ለሌሎች ታዳጊ ክልሎች ጭምር መልካም ተሞክሮ መሆናቸውን በወቅቱ የቀረበው የፌደራል ልዩ ድጋፍ ቦርድ ሪፖርት አመላክቷል።

ሪፖርቱ የክልሎችን የመንደር ማሰባሰብ ፖሮግራምና በአጠቃላይ የልማት ተግባራት አፈፃፀም በመገምገምና መልካም ተሞክሮዎች ተብለው የተነሱትን ሊበረታቱ እንደ ሚገባ በማንሳት ትኩረት በሚሹ ጉዳዮች ላይ የሁሉም አስፈፃሚና ፈፃሚ እርብርበ እንደ ሚያስፈልግም ጠቁሟል።በተጨማሪም እንደ መልካም ተሞክሮ ሆነው በሪፖርቱ ከተነሱ ጉዳዮች መካከል በኢትዮጵያ ሶማሊ  ክልል የአርብቶአደሩና ከፊል አርብቶአደሩ ማህበረሰብ ህይወት እንዲሻሻል የተከናወኑ ስራዎች በቀዳሚነት ይጠቀሳሉ።

በኢትዮጵያ ሶማሊ ክልል ከ85 ከመቶ በላይ ዜጎቹ አርብቶአደሩና ከፊልአርሶ አደሩ የአኗኗር ዘይቤን የሚከተሉ ናቸው፤ ይህ የአኗኗር ዘይቤ ደግሞ በአንድ ቦታ ላይ ተረጋግተው ከመቀመጥ ይልቅ ለእንስሳቶቻቸው የውሃና የግጦሽ ፍለጋ ከቦታ ቦታ እንዲን ቀሳሱ የሚያስገድድ ሁኔታ መሆኑን የትላንት ታሪክ ነው።በተያያዜም የክልሉ መንግስት በቀዳሚነት የህዝቡን ከማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ልማቶች ተጠቃሚ እንዲሆን በተ በታተነ መልኩ የሚኖረውን አብዛኛው የማህበረሰብ ክፍል በአንድ መንደር ማሰባሰብ መሰረታዊ መሆኑን በመገንዘብ ዘርፈ ብዙ  ስራዎች የተከናወኑ ሲሆን በተለይ ባለፉት  7ና 8 አመታት በተጨባጭ የሚታይ  ለውጥ በመመዝገብ ላይ ይገኛል።

በተለይም ማህበረሰቡን በአንድ ተሰባስቦ ከልማቱ ተጠቃሚ እንዲሆን የክልሉ መንግስት ባስቀመጠው እቅድና ፖሊሲ መሰረት የተለያዩ የመንደር ማሰባሰቢያ ማእከሎች የውሃ አቅርቦቱ በአስተማማኝነት በተረጋገጥባቸው ቦታዎች ላይ እየተቋቋሙ ሲሆን እነዚህ ማእከላት ደግሞ በዙሪያቸው የትምህርት፤የጤና መሰረተ ልማት አውተሮች እንዲ ሞላላላቸው ተደረጓል።

በ2000ዓም  በክልሉ አንድ በመንደር የማሰባሰቢያ ማእከል የነበረ ሲሆን በውስጡም ከ2ሺህ የማይበልጡ አባወራች ይኖሩበት ነበር ማእከሉም ከመሰረተ ልማት  መሟላት አንፃር አጥጋቢ ያልነበረ ሲሆን  ከ5.8 ሚለዮን በላይ ዜጎች በሚኖሩበትና  ከዚህ ውስጥ ከ80 ከመቶ በላዩ አርብቶአደር በሆነበት ክልል ይህ በፍጡም አጥጋቢ ሊሆን እንደማይችልም ግልፅ ነው። ይህን  ከ10 አመታት በፊት የነበረው ታሪክ ዛሬ ላይስ ብለን ከተጠየቀም በአሁኑ ወቅት በክልሉ ከ2 መቶ በላይ በመንደር የማሰባሰቢያ ማእከላት ያሉ ሲሆን  በመንደሮቹ ከ200 ሺህ በላይ  እማ/አባወራዎችም ከወዲያ ወዲህ የሚልኑራቸውን ሙሉ በሙሉ አቁመው በተረጋጋ ሁኔታ እየኖሩ ይገኛሉ።

በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል አንድ አባወራ በአማካኝ 6 የቤተሰብ አባላት ያቀፈበት ሲሆን በዚህ ረገድም በመንደር ማሰባሰብ መርሀ-ግብር ተጠቃሚ የሆኑ የክልሉ ነዋሪዎች ቁጥርም ከ1.2 ሚሊዮን በላይ እንደሚሆን ልብ ይለዋል።

እኒህ የማህበረሰብ ክፍሎች ኑሯቸውን ቀለል ለማድረግ እንዲቻልም ወደ 9 ሺህ የሚሆኑ የውሃ መሳቢያ ሞተሮች፤በርካታ ትራክተሮችና ምርጥ ዘሮችን እንዲያገኙ የሚደረግ ሲሆን እንደ አብነትም በተያዘው በጀት አመት በ10 ወራት ከ2000 ሺህ በላይ ዜጎች በተለያዩ የክልሉ አከባቢዎች በመንደር እንድሰባሰቡ ተችላል። በእኚህ ማእከላት ዙሪያም የጤና፤ የትምህርትና ሌሎች የመሰረተ ልማት አውተሮች ያሉ ሲሆን መንደሮቹ በጥናት ላይ ተመርኩዘው ወንዞችና እምቅ የከርሰ ምድር ዉሃ ባለባቸው አከባቢዎች የተመሰረቱ በመሆኑ ነዋሪዎቹ ወደ እርሻና ግብርና  ስራ እየገቡ ግብርናን የህይወታቸው አንድ አካል ማድረግተ ጀምሯል።

ለከብቶቻቸው የሚሆን መኖን ጨምሮ በቆሎማ ሽላና የመሳሰሉት ለም ከሆነው የክልሉ መሬት መብቀል  ከጀመሩ 10 አመታት አስቆጥሯል። ይህ በእንዲህ ማህበረሰቡን ከልማቱ ተጠቃሚ እንዲሆኑ የተከናወነው ስራዎችና አሁንም የቀጠለ ሲሆን ከጊዜ ወደ ጊዜም በመንደር የማሰባሰቡ ስራ ተጠናክሮ ቀጥሏል።ይህ የማህበረሰብ ክፍል በአንድ መንደር ሲሰባሰብ የአኗኗር ዘይቤው በተጨባጭ ስለሚቀየር በሚኖርበት ቦታ ተረጋግቶ ኑሮን እንዲላመድ የመሬት ባለቤት ይደረግና በመሬቱም ለራሱም ለእንስሳቱም የሚሆን ምርትን እያመረቱ ይገኛል።

በአንዳንድ የክልሉ አከባቢዎችም ትርፍ ምርቶች ጭምር እየተገኘ በአርብቶአደርነት የሚታወቀው ማህበረሰብ ትርፍማና አምራች እየሆነ እንደሚገኝ የማይካድ ሀቅ ከመሆኑ ባሻገር ይህን ስራ ነው እንግዲህ የፌዴራልና አርብቶ አደር ጉዳየች ልማት ሚንስቴርና የፌደራል የልዩ ድጋፍ ቦርድ ለሌሎችም ታዳጊ ክልሎች እንደምሳሌ ይሆኗል ሲል እውቅና የሰጠው።በተጨማሪም የቦርዱ ዋና ሰብሳቢና የኢፌደሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን እንደተናገሩት ስራዎቹ ከዚህም በላይ ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ያሉት።በተለይም “በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል የተከናወኑ የመንደር ማሰባሰብ ስራዎች ሊበረታቱ እንደሚገባ ቢገልጡም በአንፃሩ ደግሞ ሌሎች አርብቶ አደር በሚኖርባቸው የሃገሪቱ ክፍሎች የተከናወኑ የመንደር ማሰባሰብ ስራዎች አጥጋቢ አለመሆናቸውን አመላክተው ክልሎቹ በቁርጠኝነት” ሊሰሩ ይገባል ሲሉ ተናግረዋል

በአንዳንድ አከባቢዎች የመንደር ማሰባሰቡ ከተጀመረ በኋላ ከግብ ሳይደርስ በጅምር የሚቀርበት አግባብብዙ አያስኬድም የሚሉት  ም/ጠ/ሚኒስትሩ የአርብቶ አደሩ ህይወት መለወጥ ዋነኛ የመንግስት ትኩረት ስለመሆኑ አክለዋል።

የሚስተዋለው የእንስሳትና የሰው የመጠጥ ውሃ አቅርቦት ችግርንም በዘለቄታው ለመቅረፍ መንግስት እቅድ ነድፎ በመንቀሳቀስ ላይ ስለ መሆኑ ያነሱ ሲሆን በቅርቡም ተግባራዊ ይደረጋል ሲሉ ም/ጠ/ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ተናግረዋል:: በዚህ ዙሪያ አጭር አስደናቂ ቪድዮ እንከታተል https://youtu.be/UAzAhxlw7uc