ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ጄኔራል ሰዓረ መኮንን የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር አድርገው ሾሙ

  

አዲስአበባ(kalitimes)ግንቦት 30 ቀን 2010 ዓ.ም. የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ጄኔራል ሰዓረ መኮንን የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር አድርገው የሾሙ ሲሆን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጄኔራል አደም መሐመድ አህመድን ደግሞ የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር አድርገዋል።

በመንግስት የተለያዩ የኃላፊነት ቦታዎች ላይ ለረጅም ዓመታት ያገለገሉ ሁለት የሥራ ኃላፊዎች በጡረታ አሰናብተዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ ቀደም ሲል ወታደራዊ ማእረጋቸው ተነጥቆባቸው የነበሩት ሜጀር ጀነራል ዓለምእሸት ደግፌ እና ብርጋዴር ጀነራል አሳምነው ፅጌ ማእረጋቸው ተመልሶላቸው ከእነ ሙሉ ጥቅማጥቅም በጡረታ እንዲሰናበቱ ወስነዋል።

በተጨማሪም የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ለሀገር ውስጥ ሚዲያ እንደገለጸው፤ ከግንቦት 30 ቀን 2010 ዓ.ም ጀምሮ በጡረታ የተገለሉት በቅርቡ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባዔነታቸውን ያስተላለፉት አቶ አባዱላ ገመዳ እና በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር የነበሩት አምባሳደር ግርማ ብሩ ናቸው።

more recommended stories