የኢ.ሶ.ክ.ፕሬዝዳንት ክቡር አቶ አብዲ መሀሙድ በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል የተገኛውን ድፍድፍ ነዳጅ በይፋ አስመረቁ

 ኢለሌ(kalitimes)ሰኔ 21/2010ዓም.  የኢ.ሶ.ክ.ፕሬዝዳንት ክቡር አቶ አብዲ መሀሙድ እና ሌሎች ከፍተኛ የፌዴራልና የክልል መንግሥት ባላስልጣናት  በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል የተገኛውን ድፍድፍ ነዳጅ በዛሬው እለት በይፋ አስመረቁ፡፡

 

የድፍድፍ ነዳጅ ሀብቱ ሀገሪቱ አሁን ከገባችበት የውጭ ምንዛሬ እጥረት ለመውጣት የምታደርገውን ጥረት ለማገዝ ትልቅ አስተዋፅኦ እንዳለውም የኢፈዴሪ መንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ኃላፊ ሚኒስትር አቶ አህመድ ሺዴ ገልጿል፡፡

በተጨማሪም የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ፕሬዝዳንት ክቡር አቶ አብዲ መሀሙድ በበኩላቸው የነዳጅ ሀብቱ ለማውጣት የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ህዝብና መንግሥትም ከፍተኛ መስዋዕትነት ከፍለዋል ብሏል

%d bloggers like this: