የኦሮሞ ብሄረሰብ አስተዳደር ዋና አስተዳዳሪ አቶ እንድሪስ አብዱ ስልጣናቸዉን ለመልቀቅ ወሰኑ

ከሚሴ(Kalitimes) ሰኔ 30/2010 ዓ/ም. በአማራ ክልል የኦሮሞ ብሄረሰብ አስተዳደር ከሰሞኑ አለመረጋጋት ተከስቶ ነበር፡፡ አሁንም አርጡማ ፉርሲ ላይ የሰላም ችግሮች አሉ፡፡

አካባቢዉን ወደ ቀድሞ ሰላሙ ለመመለስም የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ገዱ አንዳርጋቸው ወጣቶችን እያወያዩ ነዉ፡፡ ከሰሞኑ ለተፈጠረዉ ግጭት እና አለመረጋጋት የብሄረሰብ አስተዳደሩ አመራሮች ኃላፊነታቸዉን አለመወጣታቸው እንደምክንት ተነስቷል፡፡የብሄረሰቡ ዋና አስተዳዳሪ አቶ እንድሪስ አብዱ የመፍትሄዉ አካል ለመሆን በፈቃዳቸዉ የመንግስት እና የህዝብን ስልጣን ለማስረከብ መወሰናቸውን ለለአማራ ብዙኃን መገናኛ ድርጅት ገልጸዋል፡፡

ዋና አስተዳዳሪዉ የብሄረሰብ አስተዳደሩን ህዝብ ይቅርታ ጠይቀዋል፡፡ የዉይይቱ ተሳታፊ ወጣቶችም ይቅርታውን ተቀብለዋል፡፡

ሰኔ 29/2010 ዓ/ም (አብመድ)

%d bloggers like this: