ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ በዓለም ባንክ የአፍሪካ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዚዳንት ሃፌዝ ግሃኔም ጋር ተወያዩ

kalitimes.co
kalitimesአዲስ አበባ(Kalitimes)ሐምሌ 3፣ 2010  የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በዓለም ባንክ የአፍሪካ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዚዳንት ሃፌዝ ግሃኔም ተቀብለው አነጋገሩ።

በዓለም ባንክ የአፍሪካ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዚዳንት ሃፌዝ ግሃኔም በኢትዮጵያ ጉብኝት ለማድረግ ነው በዛሬው እለት አዲስ አበባ የገቡት።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ለጉብኝት ወደ ኢትዮጵያ የመጡትን በዓለም ባንክ የአፍሪካ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዚዳንት ሃፌዝ ግሃኔም በጽህፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ እና በዓለም ባንክ የአፍሪካ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዚዳንት ሃፌዝ ግሃኔም በነበራቸው ቆይታም ባንኩ የኢትዮጵያ ልማትን በሚደግፍበት ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል።

እንዲሁም ኢትዮጵያ የልማት ግቦችን እንድታሳካ ባንኩ በምን መልኩ መደገፍ ይችላል የሚለው ላይ መምከራቸውንም የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ልዩ ሀላፊ አቶ ፍፁም አረጋ በትዊተር ገፃቸው አስታውቀዋል።

የዓለም ባንክና ዓለም አቀፍ የልማት ማህበር ለኢትዮጵያ የሚያደርጉት ድጋፍ 10 ቢሊዮን ዶላር መድረሱን አተፐ ፍጹም ገልጸዋል።

ይህ ደግሞ ኢትዮጵያ ከባንኩ በከፍተኛ ደረጃ ተጠቃሚ ከሆኑ የአፍሪካ አገሮች ታርታ እንደሚያሰልፋትም አመልክተዋል።

%d bloggers like this: