የኦጋዴን ብሄራዊ ነጻነት ግንባር ኦብነግ ፓርቲ አመራሮች ወደ ሃገር ቤት ተመልሰው በሰላማዊ መንገድ እንዲንቀሳቀሱ የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል አቶ አብዲ መሃሙድ ኡመር ጥሪ አቀረቡ፡፡

#(kalitimes) ሐምሌ 05፣2010የኦጋዴን ብሄራዊ ነጻነት ግንባር ኦብነግ ፓርቲ አመራሮች ወደ ሃገር ቤት ተመልሰው በሰላማዊ መንገድ እንዲንቀሳቀሱ የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል አቶ አብዲ መሃሙድ ኡመር ጥሪ አቀረቡ፡፡

ርእሰ መስተዳድሩ ይህን ያሉት ታናንት በተጀመረው የክልሉ ም/ቤት ሰባተኛ መደበኛ ጉባኤ ላይ ነው፡፡

በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ኢሶዴፓ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ደረጃ የጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ የይቅርታና መደመር መርህ ከግብ ለማድረስ በስፋት ውይይት መደረጉን  ርእሰ መስተዳድሩ ገልጸዋል፡፡

ቀደም ሲል በህዝብ ተወካዮች ም/ቤት በአሸባሪነት ተፈርጆ የነበረው ኦብነግ ከክልሉ መንግስት የቀረበለትን የሰላም ጥያቄ ተቀብሎ ወደ  ወደ ሃገር በመምጣት በሰላማዊ መንገድ ትግሉን እንዲቀጥልም  ርዕሰ መስተዳድሩ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ቀደም ሲል በክልሉ ህዝብ ላይ ለተፈጸሙ ስህተቶች የክልሉ መንግስት እና መሪ ድርጅቱ ሃላፊነት እንደሚወስድ የገለጹት የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ርእሰ መስተዳድር አቶ አብዲ መሃሙድ ህዝቡንም በይፋ ይቅርታ ጠይቀዋል፡፡

more recommended stories