የኢ.ሶ.ክ. ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሃብት ልማት ቢሮ በርካታ ሥራ አጤ ወጣቶች እየቀጠረ መሆኑ አስታወቀ

    

ጅግጅጋ(KALITIMES) ሐምሌ 13/2010 ዓ.ም በሃገራችን ኢትዮጵያ ከሚገኙት ዩኒቨርሲቲዎችና ኮሌጆች በየዓመቱ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ተማሪዎች ተመርቀው እንደሚወጡ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መረጃዎች ይጠቁማሉ።

በዚህም በሀገሪቱ ይህንን ያህል ቁጥር ያለውን የተማረ ሰው ሃይል ወደ ሥራ ማስገባት የሚችሉ የግልና የመንግሥት ተቋማትና ሥራ ኢንዱንተሪዎች አለመኖራቸው የሥራ ፈላጊውን ቁጥር እንዲበራከት ምክንያት መሆኑም ይታወቃል።

ሆኖም በዚህ ረገድ የሚታየውን የወጣቶች ስራ አጥነት ችግር ለመቅረፍ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል መንግሥት ከተለያዩ ከፍተኛ ት/ት ተቋማትና ዩኒቨርሲቲዎች ተመርቀው የሚመጡ ወጣቶችን ወደ ሥራ የማስገባት ተግባራትን እየሠራ መቆየቱ ይታወሳል።

በዚህ መሠረትም የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሃብት ልማት ቢሮ በ2011 የበጀት ዓመት በክልሉ በሚገኙት 93ቱም ወረዳዎችና 6ቱም የከተማ መስተዳድሮችን ጨምሮ ከክልሉም ሆነ ከተለያዩ የሃገሪቱ ዩኒቨርሲቲዎችና ኮሌጆች ተመርቀው ያለሥራ የተቀመጡ ወጣቶችን የሥራ ምደባና ቅጥር ፖሮግራም መጀመሩን አስታውቋል።

በተጨማሪም የኢትዮጵያ ሶማሌ ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሃብት ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ አህመድ መሀመድ በቢሯቸው በሰጡት መግለጫ ተመራቂ ተማሪዎችና ሥራ አጤ ወጣቶችን ወደ ሥራ የማሰማራት እቅድ ለክልሉ መንግሥት አዲስ ሳይሆን በማህበረሠቡ ውስጥም እንደ ጀርባ አጥንት በመሆናቸውና የክልሉ መንግሥትም ለተማሩ ወጣቶች ከሚሰጠው ልዩ ትኩረት አንጻር መሆኑን ገልፀዋል።

ከዚህ በተያያዜም “በዚህ የወጣቶች ቅጥር ዋናው ጉዳይ በወረዳዎች ላይ የሚገኙ ከተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎችና ኮሌጆች ተመርቀው እስከ አሁን የሥራ እድል ያላገኙትን እድሉን እንዲያገኙ ማድረግ ነው። በዚህ ዓመትም ሰፊ እቅድ ይዘን የቅጥር ምዝገባ ጀምረናል፤ለምሳሌ ያህልም በፋፈን፣ በጀረርና ሸበሌ ዞኖች ለሚገኙ ወጣቶች ምደባ ጀምረን የቅጥር ደብዳቤያቸውንም እየወሰዱ ይገኛሉ”ሲሉ ቢሮ ሃላፊው ተናግረዋል።

በተጨማሪም የክልሉ መንግሥት እነዚህን ወጣቶች ወደ ሥራ በማስገባት በክልሉ ሰፊ የሥራ ክፍተቶችን እንደሚሞሉና በያዝ ነው በጀት ዓመትም ለሴቶት ልዩ በመስጠት የብድር ድጋፍ መስጠቱንና የሥራ እድል ፈጠራ እንደተረገላቸውም ሃላፊው ገልጿል።

አቶ አህመድ መሀመድ አያይዘውም በተጠናቀቀው 2010 የበጀት ዓመት ታቅደው ከነበሩት መካከልም አምስት ሺህ ከተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች ተመርቀው የተቀመጡ ወጣቶችን በክልሉ የተለያዩ የሥራ ቦታዎች ለመቅጠር ታቅዶ በዚህ የአፈጻፀምም 5400 የሚሆኑትን ወጣቶች ማቅጠራቸውን አስታቋል።

ወጣቱን በሥራ እድል ፈጠራ እቅድ ተጠቃሚ ለማድረግ ሲከናወኑ የነበሩ ሥራዎች ስኬታማ እንደነበር ማየት መቻላቸውን  አክለዋል።

የሥራ ቅጥር ሲፈፅሙ የነበሩት ተመራቂዎችም የክልሉ መንግሥት ከዓመት ዓመት ለወጣቶች እየሰጠ የሚገኘው ትኩረት መልካም መሆኑንና በዚህም ደስተኛ መሆናቸውን ገልፀው፤ የክልሉን መንግሥት በሚያከናውናቸው የመልካም አስተዳደር ሥራዎች አድንቀው የላቀ ምሥጋናቸውም አቅርበዋል።

በመጨረሻም የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሃብት ልማት ቢሮ እያከናወነ የሚገኘው ከተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች ተመርቀው የመጡ ወጣቶችን በተለያዩ ወረዳዎችና ከተማ መስተዳድሮች ወደ ሥራ የማስገባት ሂደት የተማሩበትን እውቀት ወደ ተግባር እንዲቀይሩት እንዲችሉ ታሳቢ በማድረግ ሲሆን፤ የቀሩትን ደግሞ በተለያዩ የሞያ አይነቶች በማሰልጠን የክልሉ መንግሥት ሥራ ፈትነትን ለመቀነስና የተጀመረውን የልማትና እድገት ጉዞ ለማስቀጠል ከጎኑ በመቆም የድርሻቸውን ለመወጣት የሚያስችላቸው መሆኑም   ተገልጸዋል።

more recommended stories