ምግብ፣መጠጥ እና መድሀኒት አቅራቢዎች አስገዳጅ ደረጃ መግባት አለባቸው ተባለ

  

አዲስአበባ(Kalitimes)ሐምሌ 14/2010ዓ.ም. የንግድ ስርዓቱ የህብረተሰቡ ጤና ላይ ከፍተኛ ጉዳት እያመጣ በመሆኑ ምግብ፤ መጠጥና መድሃኒት አቅራቢዎች አስገዳጅ ደረጃዎችን መግባት እንዳለባቸው የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶ/ር ኢ.ር ጌታሁን መኩሪያ ተናግረዋል፡፡ ጥራትን ማጭበበር ታክስን ከማጭበርብር እጅጉን የከፋ እንደሆነ የገለፁት ሚኒስትሩ የህብረተሰብን ጤና ከመጠበቅ አንፃር ገበያ ላይ ያሉ ምርቶች ለጤና ተስማሚ እንዲሆኑ የተስማሚነት ምዘና ድርጅት ከንግድ ሚኒስቴር እና ከጤና ሚኒስቴር ጋር በቅንጅት በመስራት ለህብረተሰቡ ጥራቱን የጠበቀ ምርት ማቅርብ እንዳለበት አሳስበዋል፡፡

ማንኛውም ምርት የተስማሚነትና ምዘና የፍተሸ ስርዓት ውስጥ ማለፉ ለማህበረሰብ ጤና ለሀገር ኢኮኖሚ ያለው አስተዋፅኦ የጎላ በመሆኑ ትኩረት ሊሰጠው ይገባል ብለዋል፡፡ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ከተስማሚነት ምዘና ድርጅት ሰራተኞች እና አመራሮች ጋር በጉዳዩ ዙሪያ መክሯል፡፡ ምንጭ-ሚንስቴር መስሪያ ቤት

more recommended stories