የኢ.ሶ.ክ. መንግሥትና መሪው ድርጅት ኢሶህዴፓ በኢ/ር ስመኘው በቀለ ሞት የተሰማውን መራራ ሃዘን ይገልፃል

ጅግጅጋ(kalitimes)ሀሙስ፣ሐምሌ 19/2010ዓ.ም የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል  መንግሥትና የክልሉ መሪ ድርጅት ኢሶህዴፓ የክልሉ ፕሬዝዳንት ክቡር አቶ አብዲ መሀሙድ ዑመርን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ አመራርና ካቢኔ አባላት፣ የተለያዩ ዞኖችና ወረዳዎች አመራር አባላት፣ የክልሉ ሃገር ሽማግሌዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ ሲቪክ ማህበራት፣ የክልሉ ሄጎ ወጣቶች እና መላው የኢትዮጵያ ሶማሌ ህዝብ በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ዋና ሥራ አስኪያጅ  ኢንጅኔር ስመኘው በቀለ ሞት የተማቸውን ጥልቅና መራራ ሃዘን እየገለፁ፤ ለቤሰቦቻቸው፣ ለወዳጅ ዘመዶቻቸውና ለሥራ ባልደረባዎቹና ለመላው የኢትዮጵያ ህዝቦች መጽናናትን ይመኛል።

ኢንጂነር ስመኘው በቀለ በ1957 ዓ.ም የተወለዱ ሲሆን በበርካታ የሃገራችን የሃይል ማመንጫና የኮንስትራክሽን ልማት ፕሮጀክቶች ታሪክ የማይረሳው አሻራቸውን ያሳረፉ ጀግና የኢትዮጵያ ምሁር ሲሆኑ ዛሬ ሐምሌ 19 ቀን፤2010 ዓ.ም ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል። በዚህም ይህ ቀን በኢትዮጵያዊያን ልብ ውስጥ በታሪክ ሁሌም ሲዘከር ይኖራል።

more recommended stories