ጠቅላይ ሚኒስትሩ የተለያዩ ጥያቄዎች የሚነሱባቸውን ህጎችና አዋጆች የሚሻሻሉበት ሁኔታ በሚመለከት ‘ያገባኛል’

ዋሽንግቶን(KaliTimes)ሐምሌ 21/2010ዓ.ም. ጠቅላይ ሚኒስትሩ የተለያዩ ጥያቄዎች የሚነሱባቸውን ህጎችና አዋጆች የሚሻሻሉበት ሁኔታ በሚመለከትያገባኛልየሚል ማንኛውም አካል ሃሳቡን ማቅረብ የሚችልበት ሂደት እንደሚኖርም ጠቁመዋል።

 ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ በአሜሪካ የሁለተኛ ቀን ውሏቸው 24 ከሚጠጉ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር ሰፊ ውይይት አድርገው ከፖለቲካ ፓርቲዎቹ ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች ምላሽ ተሰጥቷቸዋል።

 አገራዊ መግባባትና እርቀ ሰላም፣ የተለያዩ ሃሳብ የሚራምዱ የፖለቲካ ፓርዎች ወደ አገር ቤት የሚገቡበት ሁኔታ እንዲሁም የተለያዩ ጥያቄዎች የሚነሱባቸው ህጎችና አዋጆችን የሚመለከቱ ሃሳቦች በፖለቲካ ፓርቲዎች ከተነሱ ጥያቄዎች መካከል ተጠቃሾች ናቸው።

 አንድነትና መግባባትን የሚሸረሽሩ ችግሮች እንደ ተጽዕኖ ፈጣሪነታቸው መጠን ደረጃ በደረጃ እንዲፈቱ የሚደረግ መሆኑን የጠቆሙት ዶክተር አብይ፤ በውጭ አገር ያሉ የፖለቲካ ፓርቲዎች ወደ አገር ቤት በሚገቡበት ሁኔታ ከኢህአፓ ለቀረበላቸው ጥያቄ የሚከተለውን መልሰዋል።

 

 

more recommended stories