ከባድ የክህደት ወን

Addisababa(kalitimes.com) 11 January, 2019. ሰውየው እጅግ በጣም ተምታቶባቸዋል በምክትል ታማጆር ሹምነት ስልጣን ይዘው የሚቀበሉትን መረጃ እንኩዋን በስርአት ካለመቀበላቸው የተነሳ ሶስት ጊዜ ሲምታታባቸው ይታያል።

የአገሪቱ መከላከያ ምክትል ታማጆር ሹም ሆነው የሚሰጡት ገለፃ አንድ ተራ የመንደር ቀበሌ ባለስልጣን ልክ ሳያጣራ በጅምላ እንደሚያነበንብ ያህል የወረደ ነው ።

ሰውየው መረጃን በሚገባ ከማጣራት ጀምሮ የቀረበላቸውን መረጃ ካለው እውነት ጋር በማመሳከር እንደ አንድ ባለስልጣን ከስሜታዊነት የራስን ድክመት ከመሸፈን ይልቅ ያለውን እውነት የታየን ሀቅ ማቅረብ ነበረባቸው።

በነገራችን ላይ የአገሪቱ ባለስልጣናት ከድሮው በባሰ ሁኔታ በይናችን ያየነውን እንኩዋን ሲገልፁት እርስ በእርሱ የሚምታታ ሌላ ክስተት አርገው ነው።

ከእኝህ ኢታማጆር ሹም በፊት የተሰጠው የመንግስት መግለጫን ተመልከቱ እና ይህ ሰውየ የሚለውን ከራሱ አፍ የተምታታ መግለጫ አስቡት.

ለዚህ ነው ኢትዮጵያ አሁንም አንካሳ አገር የሆነችው ህዝብ ያየው እውነታ ለፖለቲካ ትርፍ እና ሽፋን መጠቀም ካልቆመ ኢትዮጵያ ወደባሰ ቀውስ ውስጥ ነው የምትገባው።

ሰውየው የተምታታባቸው መሆኑን ለማየት ጭራሽ መከላከያ ሰራዊቱ የሱር ኮንስትራክሽን ማጀብ ይችላል ሲሉ የክልሉን የፀጥታ ሀይል ሀላፊነት የህገመንግስቱን ስርአት ይጥሳሉ ።

በጣም ዝቅ አሉና ጭራሽ አንተ ጋዜጠኛ አይደለህ መከላከያ እንዲያጅብህ ከፈለክ ያጅብሀል ሲሉ አሳቁን።

ከዛ ቀደም ከመከላከያ በኩል የተሰጠው መረጃ ይህ ሀላፊነት የክልሉ ፀጥታ ሀላፊነት ነው የሚል ነበር።

ትልቁ ችግር አገሪቱ ግራ በገባቸው ግራ መጋባቱዋ ነው የክልሎች የፀጥታ ሀላፊነት እንጅ መከላከያ በክልሎች ስራ ጣልቃ በመግባት ጭራሽ ድርጅቶችን አጅባለሁ ሲል ይህ የመጀመሪያው ነው።

ከዛም ቀጠሉና በቦቴ ውሀ ሊቀዱ የወጡ ወታደሮች ላይ ተኩስ ተከፈተ ያም ነው ችግር እንዲፈጠር ዋናው ምክንያት ሲሉን ይበልጥ ሲዋሹ እየን መጀመሪያ ላይ የተሰጠው መግለጫ ህዝቡ ከቦ አላሳልፍም ብሎ በነበረው ሁኔታ የሚል ነበር ዛሬ ደግሞ ፍፁም የመከላከያውን ወንጀል እራሳቸው ዘረጠጡት መኪኖቹ ተፈትሸው አልፈዋል ህዝቡም አሳልፎዋቸዋል ካሉ በሁዋላ ችግሩ የተፈጠረው ወታደሮች ውሀ ሊቀዱ ቤቴ ይዘው ሲወጡ ከሽፍቶች በተተኮሰ ጥይት ራሳቸውን ለመከላከል ነው ሲሉ ድራማውን አጦዙት አቤት ህግ አለመኖር ሰውየው ሲዋሹ እንዲህ ከሆነ ተኩሱ በሁለቱ መሀል እንጅ ህዝቡ በዛ እንዴት ሊገደል ቻለ ? የሚል ብቻ ሳይሆን ይህን ውሸት ባዶ የሚያስቀር ክስ በተመሰረተ ነበር ።

አስተውሉ ውሀ ሊቀዳ የወጣን ወታደር ላይ የመሸጉ ታጣቂወች ውጊያ ሲከፍቱ ነው ንፁሀን የተገደሉት ሲሉን ይበልጥ የሰውየው ሀላፊነት የጎደለው ንግግር ድክመት ያሳያል።

አስተውሉ ሽፍታ ያሉት ተኩዋሽ እዛው ነው ያለው ፍላጎቱ ከሆነ መግደል የመከላከያን ወታደር ከመግጠም ጋር አይያያዝም ሰውየው ጭራሽ ከድሮ ባለስልጣናት ባልተሻለ መንገድ ውሸታቸው መላ የአገሪቱን ህዝብ አሳዝኑዋል።

በተለይም በስፍራው የነበረው ህዝብ ይህን ትልቅ ውሸት ሲሰማ በእጅጉ አዝኑዋል ከዛም በላይ የምስል መረጃወች ወተዋል።

በወታደሩ እና በታጠቁት መሀል በተፈጠረ ውጊያ ሲቪላን ተጎዱ በማለት ድራማ የሰሩት ኢታማጆር ሹም ምን ያክል ህዝብን ለማታለል ቢመርጡ ነው የሚለው ያስደንቃል።

በጣም የሰውየው ውሸት አስደናቂ የሚያደርገው መከላከያ ሰራዊቱ ህፃን ሳይቀር አልሞ በመተኮስ ሲገል መታየቱ ነው ።

እንዲህ አይነት መንገድ እጅግ አስከፊ ነው በየጊዜው የህዝብ አመኔታ በጠፋ ቁጥር ህዝብ ተበድሎ በአይኑ ያየውን ለመዋሸት በተሞከረ ቁጥር እንድ አገር ወደ ባሰ ትልቅ ችግር ውስጥ እየገባች ነው የምትሄደው።

ሽፍታ አድፍጦ ከተኮሰበት ሰራዊቱ እራሱን ለመከላከል ሲል ንፁሀንን ተኩሶ የሚገልባት አገር ብቸኛዋ ኢትዮጵያ ናት።

በግልፅ የዘር ማጥፋት ወንጀል እየፈፀመ የታየን ሰራዊት እንደ አገር የመከላከያ ሰራዊት ስህተት ነው አይደገምም ተሳስተናል ብሎ በማመን ለተጎጅወች ካሳ በመክፈል ወንጀል የሰሩትን በህግ በመጠየቅ ከመጉዋዝ ይልቅ ዛሬም በከባድ ውሸት ህዝብ ተክዶዋል።

ባይናችን ያየነውን በዚህ መልኩ ለፖለቲካ ትርፍ በንፁሀን ደም በመቀለድ ጉዞ መልሶ ወደባሰ ማጥ ውስጥ የከታል።

ይህ ባደጉት አገራት ሆኖ ቢሆን ኖሮ ባለስልጣናት ከስልጣን ይወርዱ ነበር ነገር ግን አገሪቱ ኢትዮጵያ ናት ስለዚህ የንፁሀን ደም ፈሶ በፈሰሰው ደማቸውም ይነገዳል።

For how long this country will go in such a way ? How far can we go by denying such type of big scandals?

የክልሉ መንግስትስ እንዲህ አይነት ድራማ ባይናችን ያየነውን በግልፅ የተቀረፀን መከላከያ ሰራዊቱ ተኩሶ ሰላማዊ ህዝብ ሲገል ያየውን ለስልጣን ሲባል በማለባበስ መከላከያውን ሳይጠይቅ እንዴት ይጉዋዛል?

እንግዲህ ፍርዱ ለሁሉም ኢትዮጵያዊ ነው መከላከያ አገርን ህዝብን ሊጠብቅ ነው የቆመው እናም ኢታማዦር ሹሙ እራሱን ለመከላከል ሲል ንፁሀንን ከገደለ ሲል ድራማ ሰሩ ።

አስባችሁታል በሽፍታ እና በወታደር መሀል ተኩስ ሲከፈት በዚህ መሀል እራሱን ለመከላከል ህዝብን ገደለ ማረነ ።

ይሄ በራሱ ትልቅ ክህደት ነው መከላከያ ሽፍታ ሲተኩስበት ቅድሚያ መከላከል ያለበት ለህዝቡ ነው ወታደር አገርን ህዝብን ሊጠብቅ እንጅ ጭራሽ ሽፍታ ሲመጣበት ጭራሽ ህዝብን ገደለ ይህ ብቻውን ትልቅ የጦር ወንጀል እንደሆነ ሰውየውም የአገሪቱ ህግም ፍፁም ረስተዋል።

በአገሪቱ የህግ የበላይነት የለም ቢኖር ኖሮ ይህ ግልፅ የዘር ማጥፋት ወንጀል በመሆኑ የመከላከያ ሰራዊቱን በጠፈነገው ነበር ግን አገሪቱ ኢትዮጵያ ናት ወንጀለኞች ከሰሩት ወንጀል በላይ ባለስልጣናት በውሸት ክህደት ይፈፅማሉ ንፁሀንም ይገደላሉ እያለም ይቀጥላል ።

ሰውየው ባሉት እንኩዋን በሶስቱም መንገድ መከላከያው የዘር ማጥፋት ወንጀል ፈፅሞዋል የሰውየውን መልስ ተቀብለን እንኩዋን ብናይ እሽ ብለን መከላከያው ከባድ ክስ ይጠብቀዋል።

ከባድ ክህደት ወንጀል የዘር ማጥፋት

more recommended stories