የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል መንግስት በቅርቡ በምህረት የለቀቃቸው ሞዴል ታራሚዎች የዘመናዊ መኖሪያቤቶች ቁልፍ አስረክቧል

ጅግጅጋ(kaliTimes)ሰኞ፤መጋቢት 10/2010ዓ.ም.በተለያዩ ወንጀሎች ፈጽሞ በተለያዩ የክልሉ ማረሚያቤቶች ታስሮ የነበሩና በቅርቡ በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል መንግስት በምህረት ከተለቀቃቸው ታራሚዎች መካከል በእርምት ወቅታቸው ሞዴል የሆኑት ታራሚ ግለሰቦች የክልሉ መንግስት የዘመናዊ መኖሪያቤቶች  ቁልፍ አስረክቧል።

  Continue reading “የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል መንግስት በቅርቡ በምህረት የለቀቃቸው ሞዴል ታራሚዎች የዘመናዊ መኖሪያቤቶች ቁልፍ አስረክቧል”

በሸቤሌ ዞን ቀላፎ ወረዳ ነጻ የአይን ቀዶ ጥገናና ህኪምና አገልግሎት መስጠት ጀመረ

ቀላፎ (Kalitimes) ሰኞ፤ መጋቢት 4/2010

በመቶዎች ለሚቆጠሩ አይነ ብርሃናቸው የአይኖ ሞራ የተጋረዱ ዜጎች ተጠቃሚ የሚያደርገው ተንቀሳቃሽ ነጻ የአይን ቀዶ ጥገና ሃኪሞች ቡዱን በሸቤሌ ዞን ቀላፎ ወረዳ ነጻ የአይን ቀዶ ጥገና ህኪምና አገልግሎት መስጠት ጀመሩ።

ነጻ የአይን ቀዶ ጥገና ህኪምና ፖሮግራም በአጠቃላይ በኢ.ሶ.ክ.መ.አከባቢዎች የሚኖሩና አይናቸውን በአይን ሞራ የተጋረዱ እንድሁም በሌሎች ችግሮች አይነ ብርሃናቸው ላጡ ሶዎች ተጠቃሚ ያደረገና የበርካታ ዜጎች አይነ ብርሃን ያስመለሰ ፖሮግራም ሲሆን ለአንድ ሳምንት ሳምንት በቀላፎ ወረዳ ለሚኖሩና የማየት ችግር ያጋጠማቸው ዜጎች ትክረት አደርጎ በመቶዎች የሚቆጠሩ ዞጎች በተንቀሳቃሽ የአይን ቀዶ ጥገና ህኪምና ፖሮግራሙን ተጠቃሚ ያደርጋል ተብሎ እንደሚጠበቀው የወረዳው ጤና ቢሮ አስታውቋል።

በተጨማሪም የኢ.ሶ.ክ.መ.ተንቀሳቃሽ የአይን ቀዶ ጥገና ሃኪሞች ቡዱኑ ባለፎ ሳምንት በኤረር ዞን ፊቅ ወረዳ ሲያካሄዱ የነበረውን ነጻ የአይን ቀዶ ጥገናና ህኪምና አገልግሎት ማጠናቀቃቸውን ገልጿል።

በተያያዜም በቀላፎ ወረዳ አከባቢዎች የሚኖሩና አይነብርሃናቸው በተንቀሳቃሽ የአይን ቀዶ ጥገና ህኪሞች የተመለሰላቸውን ነዋሪዎች ፖሮግራሙ በከፍተኛ ደረጃ ተጠቃሚ ያደረጋቸው ከመሆኑ በሻገር የኢ.ሶ.ክ.መ. ተንቀሳቃሽ የአይን ቀዶ ጥገና ህኪሞች መድቦ በነጻ የአይን ቀዶ ጥገና ህኪምና አገልግሎት መስጠቱን አመስግኗል።

በተጨማሪም ተንቀሳቃሽ የአይን ቀዶ ጥገና ህኪምና ቡዱኑ በቀላፎ ወረዳ ለአንድ ሳምንት ያህል እንደምቆዩ አብራርተዋል።

ተንቀሳቃሽ ነጻ የአይን ቀዶ ጥገና ህኪምና ፖሮግራሙ በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል መንግስት የሚሰራ ልዩና ብቸኛ ፖሮግራም ሲሆን የክልሉ ህዝብ ተጠቃሚ ያደረገ የጤና አገልግሎት ሰጭ ፖሮግራም ነው።source:-ESMMA

*

******

የኢ.ሶ.ክ.መ.ውሃ ሀብት ቢሮ ሃላፊ በክልሉ ውሃ አገልግሎት ተደራሽነት ዙሪያ ሪፖርት አቀረቡ

ጅግጅጋ(Kalitimes)አርቢ፤መጋቢት 7/2010ዓ.ም.የኢ.ሶ.ክ.መ.ውሃ ሀብት ልማት ቢሮና የኢ.ሶ.ህ.ዴ.ፓ.ማዕከላዊ ኮሚቴ ጽ/ቤት ሃላፊ ወ/ሮ ፈርቱን አብዲ ማህዲ በጽ/ቤቷ ለክልሉ ሚዲያ አውተሮች ባለፈው 10 አመታት የክልሉ መንግስት በውሃ ሀብት ተደራሽነት ያስመዘገበው ለውጦችና በአሁኑ ወቅት በክልሉ እየተሰራ ያለው የውሃ ዝርጋታ ፖሮጀክቶች በደረሱበት ደረጃ አስመልኪቶ ለሚዲያ ማብራሪያ ሰጥቷል።
በተጨማሪም ከ10 አመታት በፊት በአጠቃላይ በክልሉ የነበረውን የውሃ ተደራኝነት ችግሮች በማስታወስ፤በአሁኑ ወቅት በከተሞች ውሃ አገልግሎትና የውሃ ልማት ዝርጋታና ተጠቃሚነትን በተመለከተ የክልሉ መንግስት በርካታ ስኬቶች ማስመዝገቡና በከተሞች የሚኖሩ የክልሉ ህብረተሰብ ተጠቃሚ ማድረግን ቢሮ ሃላፊው ገልጿል።በተያያዜም በቅርብ ርቀት የማይገኙ ወረዳዎችና ቀበሌዎች ለሚገኘው ማህበረሰብ የንጹህ መጠጥ ውሃ ተጠቃሚና ተደራሽ ለማድረግ እየተሰሩ ያሉ የውሃ ዝርጋታ ፖሮጀክቶች አበረታች ውጤቶት ማስመዝገብን ሃላፏ ገልጿል።
በሌላ በኩል በቅርብ ርቀት የማይገኙ አከባቢዎችና በቅርበት ውሃ የማይገኙባቸው አከባቢዎች ማለትም በሀጉጋ ሜዳ እስከ ጋሻሞ እየተሰራ ባሉት የንጹህ መጠጥ ውሃ ዝርጋታ ፖሮጀክቶች በአከባቢው ለሚገኙ ወረዳዎችና ቀበሌዎች እንደ ኤልበሃይ፤ቃይደርለቢሌ፤ካም ኡመር፤አኔመዶቤ፤ጋሻሞ፤ደጋህዮ አዴና አሊ ጃመዓ የሚኖሩ 78500 ሶዎችና 173,500 እንስሳትም ተጠቃሚ የሚያደርግ ከመሆኑ በዘለል በፖሮጀክቶቹ ግንባታ 216 ሚልዮን ብር የወጣበት ሲሆን ፖሮጀክቱ ለ120ኪ.ሜ.የሚያቋረጥ መሆኑንም ወ/ሮ ፈርቱን አብራርታለች።
በተጨማሪም በኢቲሻለ፤ደደመበኔ፤ኦበሻ እስከ ፊቅ በሁለት ፌስ የሚገነባ የውሃ ዝርጋታ ፖሮጀክት በኢቲሻለ-ኦበሻ አንደኛ ፌስ ብቻ በኢቲሻለ፤ቢቃ፤ሀሎቢዬ ደደበኔደዋረቶ፤አሊ ኢትዮጵያና ኦበሻ ቀበሌዎች የሚገኙ አርብቶአደርና ከፍል አርብቶ አርሶአደር ማህበረሰብን የንጹህ መጠጥ ውሃ ተደራሽ የሚያደርግ ከመሆኑ ባሻገር ፖሮጀክቱ በ156 ሚልዮን ብር የሚገነባና 19151 ሶዎችና 350 ሺ እንስሳትም የንጹህ መጠጥ ውሃ ተጠቃሚ ያደርጋል ብሏል።የንጹህ መጠጥ ውሃ ዝርጋታ ፖሮጀክቱ እስከ 150 ኪ.ሜ.እንደሚዘልቅም ቢሮ ሃላፊው አስረድቷል።

*******

ኢትዮ-ሶማሌ ክልል መንግስት በቅርቡ ለተለቀቁት ታራሚዎች መኖሪያ ቤቶች ሰጠ

ጅግጅጋ (kalitimes) ሰኞ፤ መጋቢት 10/2010

በተለያዩ ወንጀሎች ፈጽሞ በተለያዩ የክልሉ ማረሚያቤቶች ታስሮ የነበሩና በቅርቡ በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል መንግስት በምህረት ከተለቀቃቸው ታራሚዎች መካከል በእርምት ወቅታቸው ሞዴል የሆኑት ታራሚ ግለሰቦች የክልሉ መንግስት የዘመናዊ መኖሪያቤቶች ቁልፍ አስረክቧል።

ታራሚዎቹ የክልሉ መንግስት በምህረት ከተለቀቃቸው በኋላ በክልሉ የሚገኙ ኮሌጆችና ማሰልጠኛ ማዕከላት በተለያዩ የሙያ ዘርፎች ሲወስዱ የነበረው የትምህርትና አቅም ግንባታ ስልጠናቸውን አገባድደዋል።

በቀጣይም ታራሚዎቹ ከመደበኛ ማህበረሰብ ጋር በተሟላ ሁኔታ እንዲቀላቀሉ እና ከመንግስት ጠባቂ ሳይሆን ራሳቸው ስራ ፈጣሪ ለማድረግ በትላንትናው እለት የክልሉ ልዩ ፖሊስ ዋና አዛዠና የጸጥታና ፍትህ አስተዳደር ቢሮ ተጠባባቂ ሃላፊ ጀኔራል አብዱራህማን አብዱላሂ ቡራሌ እና የጅግጅጋ ከተማ ካንቲባ አቶ ኢብራህም መሀሙድ ሙባሪክ በክልሉ መንግስት በዘመናዊ መልኪ የተሰሩ የመኖሪያቤቶች ቁልፍ አስረክቧል።

ታራሚዎቹ በበኩላቸው በማረሚያቤቶች የነበሩ ወቅት የክልሉ መንግስት ስብኢና በተሞለ መልኩ ያደረገላቸው እንከብካቤና በቅርቡ ደግሞ የእርምት ጊዜያቸውን ሳያጠናቀቁ በምህረት መለቀቃቸው እንድሁም በምህረት ከተለቀቁ በሆላም የአቅም ግንባታና ግንዛቤ ማስጨበጪያ ስልጠናዎች ሰጥቶ አሁንም በዘመናዊ መልኪ የተሰሩ መኖሪያቤቶች በመስጠታቸው ደስተኛ ከመሆናቸው ባሻገር ለክልሉ መንግስት የላቀ ምስገናቸውን አቀርቧል። source:-cakaaranews.com

*

*******

በሊባን ዞን ፊልቱና ዴካ ሱፍቱ ወረዳዎች የሚኖሩ ህብረተሰብ በተዘዋወሪ ጤና አገልግሎት ሰጭ መኪና ተጠቃሚ መሆናቸውን ገለጹ

ሀየሱፍት (kalitimes) እሁድ፣ መጋቢት 9/2010

በባለፉት አመታት በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ስከናወኑባቸው ከነበሩ የልማት ስራዎች አንዱ የጤና አገልግሎት ተደራሽነትና የ ክልሉ ህዝቡ ተጠቃሚነት ለማሳደግ ሲሆን የክልሉ አርብቶ አደርና ከፍል አርሶአደር ማህበረሰብ ጥራቱን የጠበቀ የጤና አገልግሎት በማዳረስ አመርቂ ተግባራት ተከናውኗል፡፡

የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል መንግስት ጤና ቢሮ የተቀመጠለት እቅዶችና አቅጣጨዎች አንዱ በክልሉ የሚገኙት ጤና ማዕከላት ከጤና ኬላ እስከ አጠቃላይ ሆስፒታሎች ድረስ በአገልግሎትም ሆነ በሌላም ትስስር እንድኖራቸውና ለህዝቡ የጤና አገልግሎት አሰጣጥ ወደ ላቀ ደረጃ በማድረስ ነው፡፡

በዚህም በክልሉ ባጄት ከውጭ ሀገር የተገዛና በዘመናዊ መልኩ የተገጣጠመ ተዘዋዋሪ የጤና አገልግሎት ሰጪ መኪና በፊልቱና ዴካሱፍቱ ወረዳዎች ስር ከሚገኙ የሀዬ፤ሶራና ሀሙር ቀበሌዎች የሚኖሩ የህብረተሰብ ክፍሎች ከቤት ወደ ቤት ቀልጣፋ የህኪምና አገልግሎት በማዳረስ ላይ ይገኛል።የአከባቢው ማህበረሰብም ከክልሉ ጤና ቢሮ ያገኙት የህኪምና አገልግሎቱ አበረታች መሆኑን ገልጿል።

ይህ ተንቀሳቃሽ የህኪምና አገልግሎት ሰጭ መኪና የተለያዩ የህኪምና አገልጋሎትን ከቦታ ቦታ የሚያዘዋውር ሲሆን ተንቀሳቃሽ መኪናው ከሚሰጠው አገልግሎት መካከል፤ የህጻናት ክትባት፤የእናቶችና ህጻናት እንከብካቤ፤ የልጆች አልሚ የምግብ አይነቶችና የመሳሰሉትን አገልግሎቶችን ለገጠሩና ለከተሞች ማህበረሰብም እንደሚሰጥ የሀየሱፍቱ ቀበሌ ጤና ጣቢያ ዋና ስራ አስኪያጅ ወ/ሮ ነጅማ አብዱረሺድ አስረድቷል።

በተጨማሪም ይህ ተንቀሳቃሽ የህኪምና አገልግሎት ሰጭ መኪናው በውስጡ በርካታ የህኪምና መሳሪያዎች የተገጠሙ፤ ሁሉም አስፈላጊ የጤና ቁሳቁሶችና ሰው ሃይልም የተሞላለት እእንድሁም በሶለር የሚሰራ፤በገጠራማና የጤና አገልግሎት ሺፋን ቅርበት የማያገኙ አከባቢዎች ለሚኖሩ ማህበረሰብ የጤና አገልግሎት የሚያዳረስ መሆኑን የሊባንና ዳዋ ዞኖች የሪፍቱ ፖሮግራም አስተባባሪ አቶ መሀመድ ሁሴን ገልጿል።

በተያያዘም ይህ ተዘዋዋሪ የጤና አገልግሎት ሰጪ መኪና በክልሉ ገጠራማ አከባቢዎች ለሚኖሩ ማህበረሰብ ያጋጠሙ የነበረውን የጤና አገልግሎት ችግሮ ችን በከፍተኛ ደረጃ የቀረፈ ሲሆን ለገጠሩ ህዝባችን አመርቂ የጤና ሽፋን እያዳረሰ መሆኑን አይዘነጋም።

*

******

የኢትዩጲያ ሶማሌ ክልል ለተፈናቃዩች መመለስ ዋስትና የሆኑ ነጥቦች

የኢትዩጲያ ሶማሌ ብሄራዊ ክልል ላለፉት ሁለት ወራት ከክልሉ ዋና ከተማ ጅግጅጋ እና ወቻሌ አካባቢዎች የተፈናቀሉ የኦሮሞ ተወላጆችን ወደ ቀዬያቸው ሲመልስ ነበር፡፡ የክልሉ ርእሰ መስተዳደር አቶ አብዲ መሀመድ ኡመር ባሳለፍነው ሳምንት ለዛሚ ብቻ በሰጡት ቃለምልልስ አሁንም ያልተመለሱ ተፈናቃዩች እንዲመለሱ ሲጠይቁ ክልሉ ለደህንነታቸው ሀላፊነት እንደሚወስድ ተናግረው ነበር፡፡

ቅዳሜ ታህሳስ 15 ቀን ርእሰ መስተዳደሩ በጽህፈት ቤታቸው ለጋዜጠኞች ወቅታዊ ጉዳዩችን በተመለከተ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡ በወቅቱ ዛሚ ተፈናቃዩች እንዲመለሱ ጥሪ ስታቀርቡ የምትሰጡት ዋስትና ምንድነው ብሎ ጠይቋል፡፡

ርእሰ መስተዳደሩ በመጀመሪያ በወቅቱ የነበረው የፖለቲካ አለመረጋጋት አሁን ሙሉ ለሙሉ መቆሙን አስታውቀዋል፡፡ በኦሮሚያ እና የኢትዩጲያ ሶማሌ ክልሎች ወሰን ላይ የሁለቱም ክልሎች የጥበቃ ሀይሎች እንዲነሱ ተደርጓል፡፡ በምትኩም የኢትዩጲያ መከላከያ ሰራዊት ወታደሮች በተደጋጋሚ ግጭት የታየበት ወሰን ላይ ጥበቃ እያደረጉ ነው፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ሁለቱም ክልሎች የጥበቃ ሀይሎችን ከድንበራቸው አምስት ኪሎ ሜትር ለማራቅ ተስማምተዋል፡፡ ይህን ስምምነት ተላልፎ የሚገኝ የየትኛውም ክልል የጥበቃ ሀይል በሀገሪቱ ህግ መሰረት ተጠያቂ ይደረጋል፡፡

የኢትዩጲያ ሶማሌ ብሄራዊ ክልል እና የኦሮሚያ ብሄራዊ ክልል ከመኤሶ እስከ ሞያሌ ከ2ሺህ ኪሎሜትር በላይ የድንበር መስመር ይጋራሉ፡፡

በሁለተኛነት ከኢትዩጲያ ሶማሌ የተፈናቀሉ የኦሮሚያ ክልል ተወላጆች እንዲመለሱ ሀላፊነት መውሰዳችንን ያሳያል ሲሉ አቶ አብዲ መሀመድ ያስቀመጡት ነጥብ ሁለቱም ክልሎች ከሚያከብሯቸው እና ከሚቀበሏቸው የሀገር ሽማግሌዎች ጋር አብረው እየሰሩ መሆናቸውን እና ወደ ቀዬያቸው የሚመለሱትን ዜጎች በማንኛውም መንገድ ከኢትዩጲያዊነታቸው ውጪ ጽንፈኛ በሆነ መንገድ ለሚያያቸው ሰው ውግዘት እንደሚደርስበከት እና በአካባቢው ስርአት መሰረትም እንደሚጠየቅ ተናግረዋል፡፡

የእነዚህ ሁለት ክልሎች የድንበር አካባቢ ነዋሪዎች ለዘመናት በተደጋጋሚ ግጭቶች ይከሰትባቸው የነበሩ ቦታዎች ናቸው፡፡ በተለያዩ ወቅቶች የታየውም ነዋሪዎቹ እንዲጋጩ ምክንያት የነበረው ደግሞ በአካባቢው የነበረው ተፈጥሮአዊ ሀብት እና የዜጎች ፍላጎት አለመመጣጠን ነበር፡፡ ነገር ግን ከ2008 አ.ም በፊት በአካባቢዎቹየ ተከሰቱት ግጭቶች ከሀገር ሽማግሌዎች እርቅ ይፈታ ነበር፡፡ አሁን ተፈናቃዩችን ለመመለስም ወደ ቀደመው መንገድ እንደሚመለሱ ተናግረዋል፡፡

ነገር ግን ይህን ለማሳካት እንዳይቻል እና ግጭቶቹ በተደጋጋሚ እንዲከሰቱ ምክንያት ያሏቸውን ተግዳሮቶችንም አስቀምጠዋል፡፡

እንደ አቶ አብዲ ገለጻ አሁን እየተፈጠሩ ያሉት ግጭቶች ለየት ያሉ ናቸው፡፡ኢትዩጲያ ባለፉት ጥቂት አመታት የታላቁ ህዳሴ ግድብን እና ክልሎችን የሚያስተሳስሩ የመንገድ እና ሌሎች መሰረተ ልማቶችን ጀምራለች፡፡ አቶ አብዲ እነዚህ ፕሮጀክቶች የሀገር ውስጥም የውጪም ጠላት አላቸው ብለዋል፡፡ እነዚህ ጠላቶች ፕሮጀክቶችን የሚያስቆሙበት መንገድ ይፈልጋሉ፤ማንን ከማንማጋጨት እንዳለባቸው ይማከራሉ፡፡ ነዋሪዎች ደግሞ ባለማወቅ የእነዚህ ጠላት ሀይሎች መጠቀሚያ ይሆናሉ ብለዋል፡፡

ባለፉት ወራት ከኢትዩጲያ ሶማሌ እናከ ኦሮሚያ ብሄራዊ ክልሎች ባሻገር በአንዳንድ የሀገሪቱ ዩኒቨርስቲዎች ውስጥ የጉዳት መጠናቸው የተለያዩ ወደ ግጭት ያመሩ አለመግባባቶች መከሰታቸው ይታወሳል፡፡

አሁን የኢትዩጲያ ሶማሌ ብሄራዊ ክልል ርእሰ መስተዳደር አቶ አብዲ ከክልሉ ሁለት ቦታዎች የተፈናቀሉትን ዜጎች ወደ ቀዬያቸው እንዲመለሱ ጥሪ ሲያቀርቡ በሶስተኛ ደረጃ በዋስትናነት ያቀረቡት የሁለቱ ክልሎች ነዋሪዎች የአንዱ ተወላጅ በሌላው ሲኖር ከባህል እና ሀይማኖት መመሳሰል እና ቢለያዩም እንኳን ተከባብሮ በጋራ ከመኖር ባሻገር በጋብቻ የተሳሰሩ ብዙ ቤተሰቦች መኖራቸውን ነው፡፡

በኢትዩጲያ ሶማሌ ክልል የመንግስት መስሪያ ቤቶች የክልሉ ልዩ የፖሊስ ሀይልን ጨምሮ በተለያየ የስራ ደረጃ ላይ የሚገኙ በመቶዎች የሚቆጠሩ የኦሮሞ ተወላጅ ኢትዩጲያውያን ይገኛሉ፡፡

እንደ ርእሰ መስተዳደሩ መግለጫ ደግሞ ከክልሉ ቁልፍ ፕሮጀክቶች መካከል በኦሮሞ ተወላጅ ኢትዩጲያውያን ኢንጂነሮች የሚመሩት ፕሮጀክቶች በጣት ከሚቆጠረው በላይ ናቸው፡፡

አቶ አብዲ መሀመድ ተፈናቃዩችን ለደህንነታቸው ዋስትና ሰጥቶ መመለስን በተመለከተ የተናገሩት የመጨረሻ አስተያየታቸው የሚከተለው ነበር፡፡

‹‹እኛ የሚቆጨን መጀመሪያ የኦሮሞ ተወላጆች ተፈናቅለው ሲወጡ ካራማራ ላይ ቆመን በቀዬያቸው እንዲቆዩ አለመለመናችን ነው፡፡››

*********

ምንጭ:- ዛሚ ራዲዮ

ወደ ክልላችን የሚመጣ ባለሥልጣንም ሆነ እንግዳ ያለ አጃቢ በነፃነት የሚንቀሳቀስበት ሁኔታ ተፈጥሯል

የሶማሌ ክልል በፀጥታና ሰላም እንዲሁም በማህበራዊ ልማት አበረታች ውጤቶችን አስመዝግቧል።

የክልሉ ፕሬዚዳንት በ2007 ለአዲስ ዘመን በሰጡት ገለጻ በርካታ ክንውኖችን ያተቱ ሲሆን፤ ከነዚህ መሀከል የጸጥታ መሻሻል፣ የመጠጥ ውሃ ተደራሽ እና የህክምና አቅርቦት ይገኙበታል።

የክልሉ መንግሥት ርዕሰ መስተዳድር አብዲ መሐመድ ኡመር እንዳስታወቁት፤ የፀረ ሰላም ኃይሎች በሚያደርጉት እንቅስቃሴ የክልሉ ሕዝብ ለፀጥታ ስጋት ተጋልጦ ቆይቷል፡፡ ይህም በክልሉ አመርቂ የሚባል ልማት ማስመዝገብ አዳጋች አድርጎት ነበር፡፡ ካለፉት አምስት ዓመታት ወዲህ ግን የክልሉ መንግሥት በሰጠው ልዩ ትኩረትና ከፌዴራል መንግሥት ባገኘው ድጋፍ የፀረ ሰላም ኃይሎቹን በማስወገድ አስተማማኝ የሚባል ሰላም ማስፈን ተችሏል፡፡

«አሁን አሁን ማንኛውም ወደ ክልላችን የሚመጣ ባለሥልጣንም ሆነ እንግዳ ያለ አጃቢ በነፃነት የሚንቀሳቀስበት ሁኔታ ተፈጥሯል» ያሉት ፕሬዚዳንቱ፤ ለእዚህም ውጤት መመዝገብ የሕዝቡ ሚና ከፍተኛ እንደነበር አስታውሰዋል፡፡ በየደረጃው አመለካከትን የመቀየር ሥራም በመሰራቱ ፀረ ሰላም ኃይሎችን ትጥቅ በማስፈታት ወደ ሰላም እንዲመጡና የልማቱ አጋር ማድረግ መቻሉን ጠቁመዋል፡፡

በሌላ በኩልም በእቅድ ዘመኑ ከተሰሩት የልማት ሥራዎች መካከል የክልሉን ሕዝብ የመጠጥ ውሃ ተደራሽነት ለማሳደግ የተሰራው ሥራ አበረታች የሚባል መሆኑን አቶ አብዲ አመልክተዋል፡፡

እንደ እርሳቸው ገለፃ ከክልሉ ሕዝብ 85 በመቶ አርብቶ አደር ከመሆኑ ጋር ተያይዞ በውሃ እጦት ይሰቃይ ነበር፡፡ በተለይም እናቶችና ሕፃናት ውሃ ፍለጋ በሚያደርጉት ረጅም ጉዞ ምክንያት እስከ ሞት የሚደርስ ጉዳት ያጋጥማቸዋል፡፡የክልሉ መንግሥት በተለይም ባለፉት አምስት ዓመታት የሕዝቡን የመጠጥ ውሃ ችግር በመሠረታዊነት መፍታት የሚያስችሉትን መርሐ ግብሮች ነድፎ ተንቀሳቅሷል፡፡

ከእነዚህም መርሐ ግብሮች መካከልም የተፈጥሮ የውሃ አካላቶችን ወደ ልማት የማስገባቱ ሥራ ትልቅ ትኩረት የተሰጠው እንደነበር ጠቅሰው፤ በዚህም በሺዎች የሚቆጠሩ የክልሉ ሕዝቦች ተጠቃሚ መሆን መቻላቸውን ገልጸዋል፡፡ በተጨማሪም ከ480 በላይ የውሃ ጉድጓዶች መቆፈር መቻሉን ተናግረው፤ በተለይም 550 ሜትር ጥልቀት ያለውና እስከ አንድ ሺ ኪዩቢክ ሜትር ውሃ መያዝ የሚችለው የውሃ ጉድጓድ በአገር አቀፍ ደረጃ ቀዳሚ የሚያደርገው መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

ከጤና ተቋም አኳያም «ከዚህ ቀደም በክልላችን ደረጃ የነበሩትን አራት ሆስፒታሎች ወደ ዘጠኝ አድርሰናል፤ አንድ ተጨማሪ ሪፈራል ሆስፒታልም ገንብተናል» ብለዋል፡፡ በአሁኑ ወቅት የጤና ተቋማት ከዘጠኝ ሚሊዮን በላይ ሕዝብ እየተገለገለ መሆኑን አመልክተዋል፡፡ በዚህም ምክንያት ከዚህ ቀደም በወሊድ ምክንያት ይሞቱ የነበሩ እናቶችና ሕፃናትን ሕይወት ማትረፍ መቻሉን ተናግረዋል፡፡

እንደ አቶ አብዲ ገለፃ በእቅድ ዘመኑ በአጠቃላይ የተሰሩት የልማት ሥራዎች አበረታች ተብለው የሚወሰዱ ቢሆንም በተለይም አርብቶ አደሩን ወደ ከፊል አርብቶ አደር የማምጣቱ ሂደት ብዙ ሊሰራበት የሚገባ ጉዳይ ነው፡፡ ለእዚህም የሕዝቡን አመለካከት መለወጥና ግንባር ቀደም ተሳታፊ ማድረግ ይጠይቃል፡፡

************

ምንጭ:- አዲስ ዘመን – July 2015